Google Duo አሁን Google Meet ነው።
ተጨማሪ ለመረዳት

ለሁሉም ሰው የሆኑ የቪድዮ ጥሪዎች እና ስብሰባዎች።

Google Meet በማንኛውም መሣሪያ ላይ ለሁሉም ሰው የሆነ ደህንነታቸው ለተጠበቀ ባለከፍተኛ ጥራት የቪድዮ ስብሰባዎች እና ጥሪዎች የሚያገኙበት አንድ አገልግሎት ነው።

የጀግና ምስል

ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ይሰብሰቡ

Meet የሚጠቀማቸው ጥበቃዎች Google ለእርስዎ መረጃዎች ከሚያደርጋቸው የደህንነት ጥበቃዎች እና ከግላዊነትዎ መከላከያ ጋር ተመሳሳይ ነው። የMeet የቪዲዮ ጉባዔዎች በማስተላለፍ ውስጥ የተመሰጠሩ ሲሆኑ፣ የደህንነት ድርድር እርምጃዎቻችንም ለተጨማሪ ጥበቃ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይዘምናሉ።

ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ይሰብሰቡ

ከየትኛውም ቦታ ይሰብሰቡ

የንግድ ፕሮፖዛሎችን ለማቅረብ፣ የኬሚስትሪ የቤት ስራዎች ላይ ለመተባበር፣ ወይም ፊት ለፊት እንዲሁ ለመገናኘት፣ በGoogle Meet ከመላው ሰራተኞች ጋር አንድ ላይ ይሰባሰቡ።

ንግዶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች በእነርሱ ጎራ ውስጥ ላሉ እስከ 100,000 ለሚደርሱ ተመልካቾች ስብሰባዎችን በቀጥታ ዥረት ማሰራጨት ይችላሉ።

Google Meet ምንድን ነው

በማንኛውም መሣሪያ፣ ከየትኛውም ቦታ Meet

እንግዳዎች ከኮምፒውተራቸው ሆነው ማንኛውንም ዘመናዊ ድር አሳሽ በመጠቀም መቀላቀል ይችላሉ—ምንም ሶፍትዌር ሳይጫን። ከሞባይል መሣሪያዎች ሆነው በGoogle Meet መተግበሪያ መቀላቀል ይችላሉ። እንዲያውም እንግዳዎች ከGoogle Nest Hub Max ሆነው ስብሰባዎችን እና ጥሪዎችን መቀላቀል ይችላሉ።

Meet በማንኛውም መሣሪያ ላይ

በጠራ ሁኔታ ይሰብሰቡ

Google Meet በእርስዎ የአውታረ መረብ ፍጥነት ልክ ራሱን በማስተካከል፣ የትም ቦታ ቢሆኑ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የቪዲዮ ጥሪዎች እንዲኖሩ ያረጋግጣል። አዲሶቹ የAI ማሻሻያዎች፣ ያሉባቸው አካባቢዎች ባይፈቅዱም፣ የእርስዎ ጥሪዎች ጥርት ብለው እንዲቆዩ ያደርጋሉ።

በጠራ ሁኔታ ይሰብሰቡ

ከሁሉም ሰው ጋር ይሰብሰቡ

በGoogle የንግግር የማወቅያ ቴክኖሎጂ በተጎላበተው የቀጥታ መግለጫ ጽሑፍ፣ Google Meet ስብሰባዎች የበለጠ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል። የቀጥታ መግለጫ ጽሑፎች፣ ተወላጅ ላልሆኑ ተናጋሪዎች፣ መስማት ለተሳናቸው ተሳታፊዎች፣ ወይም ጫጫታ ላለባቸው ቡና ቤቶችም ቢሆን፣ ሁሉም ሊከተሏችው ቀላል ያደርጋሉ (በእንግሊዝኛ ብቻ ይገኛል)።

ከሁሉም ሰው ጋር ይሰብሰቡ
እንደተገናኙ ይቆዩ

እንደተገናኙ ይቆዩ

ያልተወሳሰበ መርሐግብር ማስያዝ፣ ቀላል ቀረጻ እና ተለማማጅ አቀማመጦች ሰዎችን በተሳትፎ እንዲሁም እንደተገናኙ እንዲቆዩ ያግዛል።

ከተሳታፊዎች ጋር ማያ ገጽ ማጋራት

ማያ ገጽዎን ያጋሩ

ሙሉ ማያ ገጽዎን ወይም አንድ መስኮትን ብቻ በማሳየት ሰነዶችን፣ ስላይዶችን፣ እና የተመን ሉሆችን ያቅርቡ።

ስብሰባዎችን ማስተናገድ

ትልልቅ ስብሰባዎችን ያስተናግዱ

እስከ 500 የሚደርሱ የውስጥ ወይም የውጭ ተሳታፊዎችን ወደ ስብሰባ ይጋብዙ።

ከስልክዎ ላይ ሆነው ይቀላቀሉ

ከስልክዎ ላይ ሆነው ይቀላቀሉ

የGoogle Meet መተግበሪያን የቪዲዮ ጥሪ ለመቀላቀል ይጠቀሙበት፣ ወይም በስብሰባው ግብዣ ውስጥ ወደ ውስጥ መደወያው ቁጥር ላይ በመደወል በኦዲዮ ብቻ ይቀላቀሉ።

ይቆጣጠሩ

ይቆጣጠሩ

ስብሰባዎች በነባሪነት ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው። ስብሰባውን ማን መቀላቀል እንደሚችል ባለቤቶች መቆጣጠር ይችላሉ፣ በስብሰባው ባለቤቶች የጸደቀላቸው ሰዎች ብቻ ሊገቡ ይችላሉ።

የክስተቶች ስርጭት

ውስጣዊ ክስተቶችን ያሰራጩ

በጎራዎ ውስጥ ላሉ እስከ 100,000 የሚደርሱ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ባላቸው እንደ የከተማ አዳራሾች እና የሽያጮች ስብሰባዎች አይነት ክስተቶችን በቀጥታ ዥረት ይልቀቁ።

መሪ ኩባንያዎች Google Meetን ያምናሉ

Colagte-Palmolive
GANT
የBBVA አርማ
የSalesforce አርማ
የAIRBUS አርማ
የTwitter አርማ
Whirlpool
የPWC አርማ

ከፍተኛ ጥያቄዎች

በGoogle Hangouts፣ Hangouts Meet፣ እና Google Meet መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

በኤፕሪል 2020 Hangouts Meet እና Hangouts Chat ወደ Google Meet እና Google Chat ዳግም ተሰይመዋል። ሁሉንም የንቡር Hangouts ተጠቃሚዎች ወደ አዲሶቹ የMeet እና የውይይት ምርቶች እንደምናዛውር 2019 ላይ አስታውቀናል። ለሁሉም ሰው በድርጅት ደረጃ የመስመር ላይ የቪድዮ ጉባዔን ለማቅረብ ሜይ 2020 ላይ ወጪ የሌለው የGoogle Meet ስሪትን አስታውቀናል።

Google Meet ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

አዎ። Meet ውሂብዎን ለመጠበቅ እንዲሁም ግላዊነትዎን ለመከላከል የGoogle Cloudን በንድፍ ደረጃ ደህንነቱ የተጠበቀ መሠረተ ልማት ይጠቀማል። ሰለ ግላዊነት ዋስትናዎቻችን፣ አላግባብ አጠቃቀም መመከቻ እርምጃዎቻችን እና የውሂብ ጥበቃችን እዚህ ማወቅ ይችላሉ።

የውጪ ተሳታፊዎች ጥሪ ሊቀላቀሉ ይችላሉ?

በሚገባ። ወጪ ለሌለው የGoogle Meet ስሪት ሁሉም ተሳታፊዎች ለመቀላቀል ወደ Google መለያ መግባት ይጠበቅባቸዋል። የGoogle መለያን በስራ ወይም በግል የኢሜይል አድራሻዎ መፍጠር ይችላሉ።

ለGoogle Workspace ደንበኛዎች አንዴ ስብሰባ ከፈጠሩ በኋላ የGoogle መለያ ባይኖራቸውም ማንኛውንም ሰው እንዲቀላቀል መጋበዝ ይችላሉ። ከሁሉም የስብሰባ ተሳታፊዎች ጋር አገናኙን ወይም የስብሰባ መታወቂያውን ያጋሩ።

Google Meet ስንት ነው የሚያስወጣው?

ማንኛውም የGoogle መለያ ያለው ሰው ወጪ የሌለው የቪድዮ ስብሰባን መፍጠር፣ እስከ 100 የሚደርሱ ተሳታፊዎችን መጋበዝ እና በአንድ ስብሰባ እስከ 60 ደቂቃዎች ድረስ መሰብሰብ ይችላል።

እንደ ዓለም አቀፍ ወደ ውስጥ መደወያ ቁጥሮች፣ ስብሰባን መቅረጽ፣ ቀጥታ ዥረት ማሰራጨት እና አስተዳደራዊ መቆጣጠሪያዎች ለመሰሉ ተጨማሪ ባህሪያት ደግሞ ዕቅዶች እና ዋጋን ይመልከቱ።

የGoogle Meet አገናኞች የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃል?

እያንዳንዱ ስብሰባ በየትኛው የWorkspace ምርት ነው ስብሰባው የተፈጠረው በሚለው ላይ የተመሰረተ የማብቂያ ጊዜ ያለው ልዩ የስብሰባ ኮድ ይሰጠዋል። ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ።

Google Meet ከእኔ የኢንዱስትሪ መስፈርቶች ጋር ተስማሚ ነው?

Google Meetን ጨምሮ ምርቶቻችን፣ የደህንነት፣ የግላዊነት፣ የተስማሚነት ቁጥጥር፣ የእውቅና ማረጋገጫዎችን ማግኘት፣ የተስማሚነት ምስክር፣ ወይም ዓለም አቀፋዊ መስፈርቶችን ማሟላቱን የሚገልፁ የቁጥጥር ሪፖርቶች፣ በገለልተኛ ወገን በመደበኛነት የማረጋገጫ ሂደት ውስጥ ያልፋል። ዓለም አቀፋዊ የዕውቅና ማረጋገጫዎቻችን ዝርዝር እና ምስክሮቻችን እዚህ ሊገኙ ይችላሉ።

የኔ ድርጅት Google Workspaceን ይጠቀማል። Google Meetን በቀን መቁጠሪያ ለምን አላየውም?

የአይቲ አስተዳዳሪዎች የGoogle Workspace ቅንብሮችን ይቆጣጠራሉ፣ ለምሳሌ Google Meet በGoogle ቀን መቁጠሪያ ውስጥ ነባሪ የቪድዮ ጉባዔ ማድረጊያ መፍትሄ መሆኑን። በድርጅትዎ ውስጥ እንዴት Google Meetን ማግበር እንደሚቻል ለማወቅ የGoogle Workspace አስተዳዳሪ የእገዛ ማዕከል ን ይጎብኙ።